Ethiopian Energy^Power Business Portal,eepBp

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive
 
 
ፎቶ፡ የኢትዮጵያ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒሰቴር
 
 
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒሰቴር ለቀጣዮች 10 መታት ከ2013 እስከ 2022 የሚያገለግለውን መሪ እቅድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት፤ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በኣዳማ ከተማ ይፋ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ይኸው እቅድ በሚቀጥሉት 10 አመታት የምግብ እና ኢነርጂ አቅርቦት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን የማየት ተልእኮን ለማሳካት የሚያስችልም ነው፡፡ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሰለሺ በቀለ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት ዘርፉ የሚመራበትን እቅድ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
 
በእቅዱም መሰረት በኢነርጂ አቅርቦትና ተደራሽነት ለፈጣን ልማትና እድገትን ለማረጋገጠ መስሪያ ቤቱ በሚቀጠሉት 10 አመታት የሚሰራቸውን ስራዎች ይፋ ባደረገው መሰረት ዘለቄታዊ ፋይናንስ ኢንቨስትመንት እና ገቢ ውጤታማ የኢነርጂ ዘርፍ ሪፎርም በማድረግ በመጭው ጊዜ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያን ዜጎች የሃይል ተጠቃሚለማድረግ ይሰራል፡፡
 
 
Related: Tracking SDG 7 Report: The Energy Progress Report 2020- Ethiopia Policy                   Case Review+ Opinion Piece
 
 
ዜጎችን የሃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በሚሰራው ስራ ውስጥም አቅምን ያገናዘበ ፍትሃዊ የአገልግሎት ተደራሽነትን ማረጋገጥ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል ጥራትና አስተማማኝነት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በማቅረብ አገራዊ ኢኮኖሚ እንዲጠናከር ማገዝ ዘለቄታዊ ፋይናንስ፤ ኢንቨስትመንት እና ገቢ ማረጋገጥ የንፁህና ኢነርጂ ቆጣቢ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ማስፋፋት እንደዋነኛ ተግባራት ተዘርዝረዋል፡፡ 
 
በመጨዎቹ 10 አመታት መስሪ ቤቱ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም በሚሰራቸው ስራዎችም ማለትም መንግስት በራሱ በሚገነባቸው የሃይል ልማት ስራዎችና የግል ባለሃብቱን በማሳተፍ በሚስሩ ስራዎች አሁን 4413 ሜጋ ዋት የደረሰውን የሃገሪቱን የሃይል ማመንጨት አቅም ወደ 20 ሺህ ሜጋዋት ለማስጠጋት ታቅዷል፡፡
በተለይ ደግሞ በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ያለውን የሃይል ተጠቃሚነት ለማሻሻል ዘመናዊ የኢነርጂ ምንጮችን በመጠቀም ተደራሽ ለማድረግ ይሰራል፡፡
በተጨማሪም ንፁህ፤ አስተማማኝና በቂ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ለሁሉም ዜጎች ማዳረስ ገጠርና ከተማ፤ በኢንዱሰትሪ ተቋማት እና ለእንስሳት የከተሞችና ገጠር ሳኒቴሽን አገልግሎት አቅርቦት ለማሻሻል ታቅዷል፡፡ 
 
የገጠርና የከተማ መጠጥ ውሃ ሽፋን 100 % ማድረስ ፤ ባለቧንባ መስመር መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በገጠር 50 % እና በከተማ ሁሉንም ተጠቃሚ ማድረግ፤ በተለዩና ድርቅ በተደጋጋሚ በሚያጠቃባቸው 100 ወረዳዎች ውስጥ ለሰዎችና ለእንስሳት የሚውል የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማድረግ የሚስችሉ ተግባራትን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰራ ይሆናል፡፡
ብሎም በኢትዮጵያ በሚገኙ 36 የተለያ ከተሞች የተቀናጀ የከተማ ሳኒቴሽን ስራዎችም ይሰራሉ፡፡ በዚህም ስራ ሰዎች በመኖሪያ ቤቶቻቸው፤ በሥራ ቦታቸውና ህዝብ በሚሰበሰብበት አካባቢ የንፁህ መፀዳጃ ቤት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በመስኖ ልማት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ በመስኖ ዘርፍ የስራ ዕድል መፍጠር፤የመንግስት ወጭ ቅነሳ እና አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን ማጎልበት ተቋማዊ አቅም እና የሰው ሃብት ልማት ማሳደግ ፤በመስኖ ልማት የስርዓተ-ፆታና አካል ጉዳተኞች አካታችነት በማሳደግ ምርትን ምርታማነትን ለማሳደግም ታቅዷል፡፡ ይህንንም ውጤታማ ለማድረግ የተሻሻሉ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም ከ2% ወደ 30% ማሳደግ በ10 ነባር የመስኖ ፕሮጀክቶች የውሃ አጠቃቀም ውጤታማነትና የሚለማ መሬት መጠን መጠቀምን ማሳደግን መሰረት ተደርጎም ይሰራል፡፡ 
 
 
Related:Tracking SDG 7 Report: The Energy Progress Report 2020 is Out--- Where Ethiopia Stands?
 
 
በመስኖ ልማት ዘርፍ በሚሰሩ ስራዎችም ለተማሩና መለስተኛ ሙያ ላላቸው ወጣቶች በዘመናዊ መስኖ የስራ እድል መፍጠር በመስኖ ጥገና፤ ግንባታ እና ተዛማጅ ስራ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር መስኖ አውታርን በማስፋፋት ለማህበረሰቡ የስራ እድል ለመፍጠር ነው የታቀደው፡፡ በተፋሰስ ልማትና ውሃ ሃብት አስተዳደር ዘርፍም የድንበርና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳይ የሀገራችንን ጥቅም 100% ማስጠበቅ የዘርፉ ዋነኛ እቅድ ተደርጎም ተቀምጧ፡፡ በውሃ ተጋሪ አገራት መካከል አብሮ የመልማት ፍላጎት ማደጉ እና ከድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት ሀገራችን ድርሻዋን መጠቀም የሚስችላትንስራዎች ለመስራት ነው የታቀደው፡፡
 
የውሃ መስኖና ኢርጂ ሚንስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ባቀረቡት በዚህ የ10 አመት መሪ የልማት እቅድ ላይ በተገለጹ ዝርዝር የልማት ተግባራት ወጣቶችንና ሴቶችን ያሳተፉ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችሉ አሰራሮችና አማራጮች በትኩረት ተቃኘተውበታል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የ10 ዓመት መሪ እቅድ የተከታተሉት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጠሮ ሃብት መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች እና የሌሎችም ቋሚ ኮሚቴ አባላትም በቀረበው መሪ እቅድ ላይ ያላቸውን አስተያየትና ጥያቄዎች አቅርበው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ፈቲሃ ዩሱፍ በተለይ በገጠርና በከተማ በሳኒቴሽን ዘርፍ የሚሰሩ ሰራዎች የቱሪዝም እንቅስቃሴው ላይ የሚፈጥሩት ተጽእኖ የጎላ በመሆኑ በትኩረት መታየት ያለበት ጉዳይ ነውም ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
 
በተጨማሪን የሃይል አቅርቦቱን ለማሻሻል በሚሰራበት ወቅት በተጓኝ የሃይል መቆራረጥን በዘለቂነት መቅፈፍ የሚቻልበት ሁኔታም ታሳቢ እንዲደረግም ጠቁመዋል።
ጉባዔው የ2013 ዓ.ም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ዕቅድ ዙርያ እንደሚመክርም ይጠበቃል።
 
 
ምንጭ፡  የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒሰቴር 
 
 
Related
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል ሽያጭ ስምምነት አደረጉ፡፡
Ethiopia zooms in on Public Diplomacy with the U.S
በኢትዮጵያ 25 ጂጋ ዋት ተጨማሪ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
Press Release: Official Virtual Launch of the Ethiopian-German Energy Cooperation and Innovation Competition on “Decentralised Energy Solutions in Ethiopia”
0
0
0
s2smodern
You are not authorised to post comments.

Comments will undergo moderation before they get published.

Comments powered by CComment

Your Energy Partners in Ethiopia>>>

eepBp tweeter Feed

eepBp Events and Calendars

October 2020
S M T W T F S
1 2 3
4 5 6 7 8 9 10
11 12 13 14 15 16 17
18 19 20 21 22 23 24
25 26 27 28 29 30 31
Book Your Travel To Ethiopia Here>>>
Afro Experience
+
Afro Experience
+
Historical Tours
+
Natural Wonders
+
Religious and Cultural Festivals
+
Travel Booking

Energy Partners>>>

On Energy

Specialized in integrated sustainable energy solutions in buildings and infrastructure projects.

read more

Green World Technologies

Specilized in marketing of renewable energy technologies in rural areas of Ethiopia.

read more

EWiEN-Ethiopian Women in Energy Network

A women in Energy association that connects and empowers Ethiopian women working in the energy sector

read more

Webinars and Active Events

No events

Join eepBp Community